የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች ከሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች መካከል በዋናነት፡- ከህመሙ እና ተያያዥነት ካላቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች ጋር መኖር፣ ጥራት ያለውና የማያቋርጥ የሕክምና አቅርቦት አለመኖር፣ የመድኃኒት ዋጋ ንረት እና የአቅርቦት ውስንነት፣ እንዲሁም መገለልና መድልዎ ናቸው፡ ኬርኤፕለፕሲ ኢትዮጵያ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመቅረፍ እንዲሁም የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች ጤናማ፣ አምራች፣ ከመገለልና መድሎ ነፃ ሆነው ማየት የሚል ራዕይ ይዞ የሚጥል ህመምን ትኩረት አድርጎ በኢትዮጵያ በጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም የተቋቋመየመጀመሪያው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡