Advocacy Initiatives

Our advocacy program collaborates with stakeholders to influence policies and improve services for people with epilepsy and associated conditions. 

Key aspects of our advocacy work include:

  • Empowering Voices: Encouraging individuals with epilepsy to advocate for their needs.
  • Policy Advocacy: Influencing government policies and practices targeting primary healthcare providers, the Ministry of Health, local leaders, non-state actors, state actors, and key health stakeholders.
  • Partnerships: Engaging with neurologists, private entities, community associations, and charities to address epilepsy needs.
  • Community Engagement: Working with community leaders and traditional healers to build support and understanding.
  • International Collaboration: Partnering with global organizations to amplify our advocacy efforts.


ለታማሚዎች መብት መሟገት እና ድርጅታዊ ግንኙነቶችን ማዳበር
ኬርኤፕለፕሲ ኢትዮጵያ የሚጥል ህመም ታማሚዎች ላይ በሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ዙሪያ ድምፃቸው እንዲሰማና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበር ከህብረተሰቡ አባላት ጋር በመሆን ትክክለኛ መሠረት ያደረገ አቀራረብን እና ድጋፍን ከፍ በማድረግ ጠንካራ ተሟጋችነቱን አሳይቷል፡፡
ድጋፍ ሰጭ ቡድን (የህሙማን ተወካዮች) መመስረት
የችግሩ ባለቤት የሆኑትን የሚጥል ህመም ህሙማንና ቤተሰቦቻቸውን ተሳትፎ ለማጎልበት፣ ታማሚዎች በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት በመድሃኒት አቅርቦትና በጤና ባለሞያዎች የሚገጥማቸዉን የአሰራር ችግሮች እንዲፈቱ ለመስራትና በሚጥል ህመም ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለመቀየር እንዲሁም ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ ምክክሮችንና ግንዛቤዎችን ለመስጠት ድርጅቱ ህሙማንና ቤተሰቦቻቸውን አሰባስቦ ትርጉም ያለው ተጨባጭ ለዉጥ ለማምጣት እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል፥ መርሃ ግብር የሚያሰናዳ ድጋፍ ሰጭ ቡድን (የህሙማን ተወካዮች ኮሚቴ) ጥቅምት 25/2010 እንዲቋቋም አድርጓል።
ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር መሥራት
በኢትዮጵያ በሚጥል ህመም ዙሪያ ላሉ ችግሮች መፍትሄዎቹ በጣም የተወሳሰቡና አንድ ድርጅት ብቻዉን ሊፈታው የማይቻል ነው፡፡ ስለሆነም ኬርኤፕለፕሲ ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት፣ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማመንጨት እና መፍትሄዎችን ለማምጣት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ በበጎ አድራጎት አገልግሎት ላይ ከሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሁልጊዜም ግንኙነቱን አጠናክሮ በትብብር ይሠራል፡፡ ይህንንም የምናሳካበት ስትራተጂ፡-
ትኩረት ለሚጥል ህመም እንዲሰጥ እና ለህሙማኑ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ከህመሙ ተጠቂዎች እና ከህመምተኛዉ ቤተሰቦች ጋር በመተባበር፣የሚጥል ህመም ህክምና እንዲስፋፋ፣ በበቂ ባለሙያዎች እንዲሰጥና የመድሀኒት አቅርቦት ችግር እንዲቀረፍ ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ ከክፍለ ከተማና ወረዳ ጤና ጽ/ቤቶች፣ ከሆስፒታሎች፣ ከክልል ጤና ቢሮ፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ ከሚገኙ ጤና ተቋማት ጋር ሰፊ ግንኙነት በመፍጠር እና በጋራ በመስራት፣በሚጥል ህመም ላይ ያለዉ የተሳሳተ አመለካከት እንዲለወጥ የቅስቀሳ ስራዎች፣ ስልጠናና ትምህርት ለተለያዩ አጋር ድርጅቶች ለምሳሌ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የማህበረሰብ አቀፍ ተቋማት፣ የኢትዮጵያ የነርቭ ሐኪሞች ማህበር፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የግል ድርጅቶች፣ ቤተ እምነቶች፣ መገናኛ ብዙሀን እና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመስጠት ነው፡፡